About Us

ውድ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናችሁ የዳናችሁ ክርስቲያኖች

ይህን ገፅ ስንከፍት “እንደቢሆኑልን” ትልም ይዘን የተነሳነቸዉ ጉዳዮች መኖራቸው አያጠራጥርም። በዚህ ገፅ በሚንሸራሸሩ እሳቤዎች ውስጥም እንደግብ የያዝናቸውን አንኳር መልዕክቶች እዚህም እዚያም ታገኟቸዋላችሁ።

በየደቂቃው በሚለዋወጥ አለም የመኖራችንን ያህል፥ ጥሞና እና ማሰላሰል የሚወደውን አዕምሮአችንን ዕረፍት የሚነሱ፤ ሲያሻቸው በደስታ የሚያሰክሩን ፤ ሳንፈልግ በሀዘን ማጥ የሚከቱን ክስተቶች አያሌ ናቸው። ከዚህ በከፋም ዘወትር በሚያድግ ፈጠራ የታጀበው ገበያዋ ፍላጎታችንን እጅግ ለጥጦ ከፍተኛ የምኞት አለም ውስጥ ከትቶናል።

ለአንድ ህይወቱ ከምድር ያለፈ ተስፋ ለሌለው ግለሰብ ይህ ጥሩ ነው። በምን ላድርግ እና በምን ልሁን ሳይጨነቅ፤ በምድር ያየውን እየተመኘ፥ ምኞቱን እስኪያሳካ ጊዜያዊ ተስፋ እየሰነቀ የምድር ቆይታውን የተሻለ ያደርጋል።

ለክርስቲያንስ? ክርስቶስን መስሎ በመኖር የዘላለም ህይወት ተስፋውን ለማሳካት ለሚጥረውስ? ይህ የአለም “መልካም መሳይ” ወከባ እንቅፋት ነው። መጠን የለሽ አቅርቦቷ፥ በመጠን ኑሩ የሚለውን የ ክርስቶስ ምክር የሚያዘነጋ ነው። የገንዘብ ኃይሏ፥ ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም የሚለውን መመሪያ የሚጣረስ ነው። እናም ከዚህ ምድር የሚሻገር ተስፋ ሰንቆ የተነሳው ክርስቲያን ተጓዥ፤ ምድር ላይ ያሉ ትንንሽ እንቅፋቶች አደናቅፈውት ዳተኛ ሆኖ ይቀራል።

አላማችን ይህ ነው፦ በፁሁፎቻችን ሁሉ ተስፋ እስኪሞላ እና ክርስቶስ እስኪገለጥ፤ እኛ ክርስቲያኖች ፈላሲ እንጂ ከታሚ አለመሆናችንን ማስገንዘብ፤ ተስፋችን ከዚህ ምድር የሚሻገር በመሆኑ እንቅፋት በበዛበት ጎዳና ዳተኞች እንዳንሆን በተስፋ ማበረታታት ነው።