በአምስቱ ጣቶች ምሳሌነት መፀለይ

በአማኝ ህይወት ውስጥ ፀሎት እና ቃለ እግዚአብሔር ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ እንደ ቅዱ ቃሉ ምክረ ሳብ መሰረት  ክርስቲያን ጸሎቱ የማይቋረጥ ሊሆን ይገባዋል፡፡ የፀሎት ህይወትን ሊያነቃቃ ይችላል ብለን ያሰብነውን ልናካፍላችሁ ስናስብ በአምስቱ ጣቶች ምሳሌነት መፀለይ የሚለው ተምሳሌታዊ መርህ የተሻለ ሆኖ ስላገኘነው እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

አውራ ጣት፡- አውራ ጣት ከሁሉም ጣቶቻችን ለእኛ የሚቀርበን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥንካሬን የሚሰጠን ነው፡፡ ስለዚህ ፀሎታችሁን በህይወታችሁ ውስጥ ቅርብ ለሚባሉት ሰዎች በመፀለይ ጀምሩ፡፡ ይህ አስደሳቹ ሀላፊነት ነው፡፡ ለወላጆች፣ ለትዳር አጋር.፣ ለልጆች እና ለቅርብ ጓደኞች በመፀለይ ጀምሩ፡፡

በቻይና የሚገኘው እና ኤርሊ ሬይን ኮቨናንት ምዕመናን ፓርክ ውስጥ ተሰብስበው ማምለክ ጀመሩ፡፡

ጠቋሚ(ሌባ) ጣት፡- ጠቋሚ ጣት ሁሌም የሚመሩንን፤ የሚያዙንን እና የሚያሰለጥኑን ያስታውሰናል፡፡ ጸሎታችሁን ለመምህራኖቻችሁ፣ ለስራ አለቆቻችሁ፣ ለአገልጋዮቻችሁ በ መፀለይ ቀጥሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከእናንተ ህይወት በተጨማሪ በሌሎችም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው ለእነርሱ በመፀለይ ብዙዎችን መጥቀም ይቻላል፡፡

መሀል ጣት፡- መሀል ጣት ከሁሉም ጣቶቻችን ዘለግ ብለው የሚታዩ እና አይነ ግቡዎች ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ ጣታችን መሪዎችን ሊያስታውሰን ይችላል- ምክንያቱም ከሁላችንም ገነን ብለው እነርሱ ይታያሉና! ስለ መሪዎች መፀለይ ለሀገር መፀለይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም በተደጋጋሚ መልካምም ሆነ ክፉ ለሆኑ መሪዎች እንድንጸለይ ይመክረናል፡፡ ስለዚህ ፀሎታችን መሪዎችን ያካትታል ማለት ነው፡፡

ቻይናዊው መጋቢ ከመታሰሩ በፊት የፃፈው ደብዳቤ

ቀለበት ጣት፡- ብዙዎቻችን አስተውለነው ባናውቅም የቀለበት ጣት ከሁሉም ጣቶቻችን ይልቅ ደካማዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ በፀሎታችን ስለደካሞች ልንማልድ ይገባናል፡፡ በመከራ ላሉት፤ በጭንቅ እና በህመም ለሚሰቃዩት ልንፀልይ ይገባል፡፡ ምክንያቱም እነርሱም በክርስቶስ የእኛ አካል ናቸውና፡፡

ትንሿ ጣት፡- ይቺ ጣታችን ከሁሉም የምታንስ በመሆኗ እራሳችንን ልታስታውሰን ይገባል፡፡ ሁላችንም ባልንጀራችን ከእኛ የሚሻል አድርገን የምንቆጥር ክርስቲያኖች እስከሆንን ድረስ ትንሿ ጣት ከእራሳችን የተሻለ ማንም ልትወክልልን አትችልም፡፡ ስለዚህ ለእለት እንጀራ የሚያስፈልገንን ሁሉ፤ በይበልጥም ደግሞ ስለመንፈሳዊ እድገታችንን ለራሳችን ልንፀልይ ይገባል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *