በቻይና የሚገኙ ምዕመናን ፓርክ ውስጥ ተሰብስበው ማምለክ ጀመሩ፡፡

በቻይና የሚገኘው እና ኤርሊ ሬይን ኮቨናንት(Early Rain Covenant) እየተባለ የሚጠራው የወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የቤተክርስቲያናቸውን መዘጋት ተከትሎ ፓርክ ውስጥ ተሰብስበው ማምለክ መጀመራቸው ተነገረ፡፡ ከቀናት በፊት መጋቢያቸውን ጨምሮ 100 አባሎቻቸው በመንግስት ሀይሎች ታስረው ማምለኪያ ቦታቸው በብረት ተዘግቶባቸው ነበር፡፡ ቤተክርስቲያናቸው መዘጋቱን ያላወቁ አማኞች ወደቦታ ቢያመሩም በሮቹ በሙሉ በብረት ተበይደው እና ተዘግተው ያገኟቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ተሰብስበው በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ፓርክ በማምራት ማምለክ እና የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መጋራታቸውን ቀጥለዋል፡፡

መምህሩ ሴቷን ወንድ ብዬ አልጠራም በማለቱ ተባረረ፡፡

ድፍረታቸው እና የእምነታቸው ፅናት ብዙዎችን ያስደመመው አማኞች ፌስቡክ ላይ የተለቀቀው ቪዲዮ እንደሚያሳየው መዝሙር 43፡ 4 ላይ ያለውን “እኔም ወደእግዚአብሔር መሰዊያ አቀናለሁ፤ ፍጹም ደስታዬ ወደሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ በበገና አመሰግንሃለሁ፡፡” የሚለውን በጋራ ሲዘምሩ ነበር፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቷ ደጆች በብረት የተዘጉ እና ብዛት ባላቸው ወታደሮች የሚጠበቅ ከመሆኑ የተነሳ ማንም መግባት እንደማይችል በአካባቢው ያሉ አማኞች ተናግረዋል፡፡  ኤርሊ ሬይን ኮቨናንት የተባለውን የአማኞች ስብስብ ከመሪያቸው ጋር ለእስር የዳረጋቸው በቻይና መንግስት ፍቃድ አለማግኘታቸው እና ሶስቱ ራሶች ቤተክርስቲያን(three self Chruch) በሚባለው ባለመታቀፋቸው ነው፡፡ ይህ ሶስቱ ራሶች ቤተክርስቲያን (three self Chruch) የሚባለው በቻይና ውስጥ የሚገኙ ከ60,000 በላይ የሚሆኑ ቤተክርስቲያኖች ስብስብ ሲሆን መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሳይቀር የ ኮሚኒስምን ፕሮፖጋንዳ በማስገባት ክርስትናን መሰረቱን በማጥፋት እና ከቻይና ባህል፤ ሀይማኖት እና ፖለቲካ ጋር ለመቀላቀል የሚጥር የመንግስት አካል ነው፡፡ የትኛውም ቤተክርስቲያን ሶስቱ ራሶች ቤተክርስቲያን(three self Chruch)  የሚባለውን ማህበር ካልተቀላቀለ ህጋዊ መሆን ካለመቻሉም በላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ መከራ ይጠብቀዋል፡፡ ሶስቱ ራሶች ቤተክርስቲያን (three self Chruch)  ስያሜውን የወሰደው ራስን መግዛት፤ ራስን መደገፍ እና  ራስን ማስፋፋት ከሚለው የሶስቱ ራሶች(three self’s) ፅንሰ-ሀሳብ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም የዚህች ቤተክርስቲያን መጋቢ ከመታሰሩ በፊት ግሩም መልዕክት ያለው ደብዳቤ ፅፎ በበጎ ፈቃደኞች ተተርጎሞ በ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲራጭ ነበር፡፡ በፓርኩ ውስጥም የአምልኮ ስነስርዐቱን መርታችኋል የተባሉ ሶስት ሰዎችም በፖሊስ ተይዘው ወደእስር ቤት ተወስደዋል፡፡ ይህም የታሳሪዎችን ቁጥር ወደ 103 አሳድጓል፡፡

እለት ተዕለት መከራን በመቀበል ላይ ለሚገኙት የቻይና አማኞች እንድንፀልይ የፈላሲ ህብረት በፅኑ ያሳስባል፡፡

One thought on “በቻይና የሚገኙ ምዕመናን ፓርክ ውስጥ ተሰብስበው ማምለክ ጀመሩ፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *