እዩት፤ እሱም አብሮኝ ያለቅሳል፡፡

የዮሐንስ ወንጌል 11፡-32-35

32 ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ፡፡ ጌታ ሆይ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞትም ነበር አለችው፡፡

33 ኢየሱስም እርስዋ ስታለቅስ ከእርስዋም ጋር የመጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ በመንፈሱ አዘነ በራሱም ታወከ፤

34 ወዴት አኖራችሁት አለም፡፡ እነርሱም፡-ጌታ ሆይ መጥተህ እይ አሉት፡፡

35 ኢየሱስም እንባዉን አፈሰሰ፡፡

ስለ መለኮታዊ ፍትህ የምንጠይቅበት ጊዜ አለ፡፡ ነገሮችን መሸከም አቅቶን በፈተና የምንዝልበት፤ የእግዚአብሔርን እርዳታ ሽተን ስንጠራው “የሚዘገይ” የሚመስልበት ጽልመት፡፡ የሀዘን ሸክም ብርክ አስይዞን በእንባና በምጥ አምላክን ስንጠራ ዝም ያለባቸው  ሌሊቶች ፤ አጥንትን አልፎ እንደሚሰረስር ቁር ሰውነትን የሚያደነዝዝ ፍርሀት ሲወረን . . .ይሄ ሁሉ ሲሆን እሱ የታለ?

የመከራ ግርዶሽ የእምነት አይናችንን ጋርዶን ለስቃያችን የሚገደው ባይመስለንም- የሚሆንብንን የመዐት ናዳ እየተመለከተ የሚዝናና አምላክ ግን አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ መሞት እንደነበረበት “አልዐዛር” ነገራችን የግድ ቢሞትም፤እንደነማርታ እና ማሪያም “ብትኖር ኖሮ እኮ” በሚያስብል ሰዐት ቢደርስም- እዩት፤ እሱም አብሮኝ ያለቅሳል!! “እኔ ከከበርኩ ቢያዝኑና ቢያለቅሱ ምን ገዶኝ!” በሚል ስሜት ሳይሆን ከፍቃዱ የተነሳ በሚደርስብን መከራ የነገሩን ከባድነት በሚረዳ መንፈስ እሱም አብሮን ያዝናል፡፡

የሂልሶንግ አምልኮ መሪ ዳርሊን ዤክ አስገራሚ የህይወት ታሪክ የሚያትት መፅሐፍ ለንባብ በቃ!

One thought on “እዩት፤ እሱም አብሮኝ ያለቅሳል፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *