“እንደቤትህ ቁጠረው”

የእንግድነት ስሜትን አትንኖ የሚያጠፋ፤ ከሰዎች ጋር ቶሎ ሊቀርቡ የሚሹ ተግባቢ ሰዎች ግብዣ-እንደቤትህ ቁጠረው፡፡ ይህን ቃል ከሰማህበት ቅፅበት አንስቶ ላይህ ላይ የተመረገው ጭንቀት ሁሉ ይጠፋል፡፡ በዝምታ የሸበበህን ቤት በሁካታ ትሞላዋለህ- በአደብ የያዘህን እልፍኝ አልፈህ ጓዳ ድረስ ትዘልቃለህ፡፡ በቤቱ ውስጥ የእኔነት ስሜትህ…

እዩት፤ እሱም አብሮኝ ያለቅሳል፡፡

የዮሐንስ ወንጌል 11፡-32-35 32 ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ፡፡ ጌታ ሆይ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞትም ነበር አለችው፡፡ 33 ኢየሱስም እርስዋ ስታለቅስ ከእርስዋም ጋር የመጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ በመንፈሱ አዘነ በራሱም ታወከ፤ 34 ወዴት አኖራችሁት…

ቆይታ በገሃነም

ተመልሰው ላይከፈቱ የተዘጉ የሚመስሉ አይኖቼን በቀስታ ገለጥኳቸው፡፡ ከፍተኛ ድካም ተሰምቶኛል፡፡ ከወደቅሁበት ተነሳውና ልብሴ ላይ ያለውን አሸዋ በእጆቼ አራገፍኩ፤ ሰውነቴ ድቅቅ ብሏል፡፡ የት ነው ያለሁት? ዙሪያውን ለመቃኘት ድካም የሰበረው አንገቴን አዙሬ አማተርኩ. . .ድንግዝግዝ ያለ ቦታ ነው፤ ፀሃይ አትታይም፣ ጨረቃም የለችም…