መምህሩ ሴቷን ወንድ ብዬ አልጠራም በማለቱ ተባረረ፡፡

በቨርጂኒያ የሚገኘው ዌስትፖይንት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆነው ፒተር ቭሌሚንግ ጾታዋን ከሴት ወደወንድ የቀየረችውን ተማሪ በወንዴ ፆታ አልጠራም በማለቱ ምክንያት ተባረረ፡፡ የትምህርትቤቱ ተቆጣጣሪ እንዳስታወቀው መምህሩ ተማሪዎችን በማንነታቸው በማግለል ምክንያት መባረሩን አስታውቀዋል፡፡

በአምስቱ ጣቶች ምሳሌነት መፀለይ

“ይሄ ሰውን በማንነቱ ማግለል የመማር ማስተማር ሂደቱን ያውካል፤ ተማሪዋም ይሄን ገልፃለች- ወላጆችዋም ሳይቀር ይሄን ገልፀዋል” ያለው ሀላፊው የመምህሩ መባረር ተገቢ ነው ብሏል፡፡ወንጌላዊ አማኝ እና የፈረንሳይኛ መምህር የሆነው ፒተር “ሴት ለነበረች፤ በራሷ ፍቃድ ወደወንድነት የተቀየረችን ሴት ወንድ ብዬ ለመጥራት ህሊናዬ አይፈቅድልኝም ነገር ግን ለራሷ የሰጠችውን የወንድ የስም ስያሜ ተቀብዬ እየጠራኋት እገኛለሁ” ብሏል፡፡

ይህን ዜና ተከትሎ በመላው አሜሪካ ቁጣ የተቀሰቀሰ ሲሆን መባረሩን በመቃወም የፊርማ ማሰባሰብ ስርአት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የመምህሩ ጠበቃ በበኩሉ ይሄ ለማንኛውም አሜሪካዊ የተሰጠውን ህሊናው የሚከለክለውን ያለመናገር መብት የሚጻረር መሆኑን ለሚዲያ ገልጧል፡፡

One thought on “መምህሩ ሴቷን ወንድ ብዬ አልጠራም በማለቱ ተባረረ፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *