በመጠን መኖር

ክርስትና እምነት ነው። እምነት ደግሞ ተስፋን የሚያረጋግጥ፤ የማናየውን የሚያስረዳ ነው፦ ይህ ማለት ክርስትና ተስፋን ለማግኘት የሚደረግ የምድር ጉዞ ነው። ተስፋው ከቶውን በምድር የማይገኝ፤ ይልቁንም ሞትን ተሻግሮ የተቀመጠ የዘላለም ህይወት ለሆነ አማኝ፥ በምድር ላይ ሲኖር ፈተናው የገዘፈ ነው። በእምነት የሚመለከተውን ተስፋ፤ በአይኑ ፊት የሚደቀን የስጋ ምኞት ይጋርድበታል። እጅግ የከበረውን የዘላለም ማንነት፤ በስባሽ ስጋው ያጨነግፍበታል። ለዚያም ነው በቅዱስ ቃሉ በተደጋጋሚ በምድር ላይ በመጠን እንድንኖር የሚመክረን።

ቀጣዩን ክፍል እዚህ ያግኙ!

የዐለም ኑሮ ቀላል አይደለም። በሰውነታችን የሚካሄድ የስጋ እና የመንፈስ ውጊያም እንዲሁ። እናም የዚህ ምድር አታላይ ምኞት በተስፋችን ላይ ሲያይል ቅዱስ ቃሉን እንደምኞታችን መቃኘት እና ማበጀት (customize) እንሻለን። በተለይም ጠንከር ያለ መልዕክት ያላቸው ክፍሎች የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች ናቸው። “በመጠን ኑሩ” የሚለው ቃል የዚሁ ድርጊታችን ሰለባ የመስለኛል። “በመጠን ኑሩ” ይላል እንጂ መጠኑን እንለካው ዘንድ በሜትር እና በሊትር አላስቀመጠልንም። ገርበብ ብሎ እንደተከፈተ በር የተቀመጠ በመሆኑ ምኞታችን እና የአይን አምሮታችን በገዘፈ መጠን ይህን ቃል ለማለዘብ መሞከራችን የማይቀር ይሆናል።

ሶስተኛውን ክፍል እዚህ ያንብቡ!

🤔መጠኔ ስንት ነው?

ቅዱሱ መፅሀፍ በምድራዊ መለኪያ የተሰፈረ እና እንደኦሪታዊ ስርዐት የመጠን ህግጋትን ያካተተ የኑሮ መርህ ባይሰጠንም፥ በመጠን መኖር እስከምን ድረስ፤ መጠንን ማለፍ ደግሞ ከየት ጀምሮ መሆኑን ያስረዳናል።

⚠️በቀጣይ ክፍል “መጠኔ ስንት ነው?” በሚል ርዕስ አብረን ቆይታ እናደርጋለን፡፡ እስከዚያው ግን እርስዎ በመጠን መኖር ስለሚለው ቃል ያሎት ሀሳብ ምንድነው? ምን ምንን ያካትታል? በኮሜንት ላይ ሀሳብ እና አስተያየትዎን ያካፍሉን፡፡

2 thoughts on “በመጠን መኖር”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *