በመጠን መኖር–እስካላንቀላፋን ድረስ

#ክፍልሁለት 📌ከመጣጥፉ ጋር ሊነበብ የሚገባው የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል 📋1ኛ ተሰሎንቄ 5:1-9 አንደኛው በመጠን የመኖር ልኬት አለማንቀላፋት ነው፡፡ በመጠን የሚኖር ክርስቲያን አያንቀላፋም። ይልቁንም ዘወትር በንቃት የተስፋውን መገለጥ ይጠባበቃል እንጂ። በክርስቶስ ያመንን አማኞች የማናንቀላፋው ህይወታችን ሁሌም በብርሀን የተሞላ በመሆኑ ነው። የሚያንቀላፉ በሌሊት…

በመጠን መኖር

✅ክርስትና እምነት ነው። እምነት ደግሞ ተስፋን የሚያረጋግጥ፤ የማናየውን የሚያስረዳ ነው፦ ይህ ማለት ክርስትና ተስፋን ለማግኘት የሚደረግ የምድር ጉዞ ነው። ተስፋው ከቶውን በምድር የማይገኝ፤ ይልቁንም ሞትን ተሻግሮ የተቀመጠ የዘላለም ህይወት ለሆነ አማኝ፥ በምድር ላይ ሲኖር ፈተናው የገዘፈ ነው። በእምነት የሚመለከተውን ተስፋ፤…

ሌላው አንጻር

“የቄሳርን ለቄሳር፤የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር” የሚለው ተረስቶ ቄሳር እና እግዚሀር የጋራ ንዋይ ባፈሩበት በዚህ ዘመን- ሀይማኖት እና ንግድ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች፤የፍቅር ትምህርት እና የራስ ወዳድነት ግብር ባልንጀሮች ቢሆኑ አይደንቅም፡፡ ከሁለት ሺህ አመታት በፊት በጅራፍ እየገረፈ ያስወጣቸው ነጋዴዎች ረጅም አመት በፈጀ የትጥቅ…

ክርስቶስ በጣቱ ምን ጻፈ?

ይህን የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ በማነብበት ጊዜ ሁሉ እጅግ መደነቄ የማይቀር ነው፡፡ ምናልባትም በገጠራማዋ ገሊላ ይልቁንም በዚች የወይራ ዛፎች ኮረብታ በምትሆን ደብረ ዘይት መንደር ውስጥ የሆነው ሙግት መጪውን የሰው ልጅ እጣ ፈንታ አስቀድሞ የሚያመለክት በመሆኑ ይሆናል፡፡ ውብ ማለዳ ነበር-በተራራማዋ የወይራ ዛፎች…

ዝለት

(ዝለት) በወንጌል አ. መሻት እና ምኞት በሰው ልጅ ህይወት ታሪክ በሙሉ ረግተው አያውቁም፤ ዘወትር ሞገደኞች ናቸው፡፡ ሀይላቸውም ያን ያህል ነው-እጅግ ተራ የሚባል መሻታችን ነፍሳችንን እንዳልተገራ ፈረስ፤ መንፈሳችንን መልህቅ እንደሌለው መርከብ ወዲያና ወዲህ ሊንጠው ይችላል፡፡ ከየት እንደመነጨ የማናውቀው ምኞት ቅጽበታዊ በሚመስል…